am_tn/luk/09/61.md

1.6 KiB

እከተልሃለሁ

“ደቀ መዝሙር እሆናለሁ” ወይም “አንተን ለመከተል ዝግጁ ነኝ”

በመጀመሪያ በቤቴ ያሉትን እንድሰናበታቸው ፍቀድልኝ

“ያንን ከማድረጌ በፊት በቤቴ ላሉት ሰዎቼ ልሄድ መሆኔን እንድነግራቸው ፍቀድልኝ”

ማንም … ለእግዚአብሔር መንግሥት ብቁ

ኢየሱስ የእርሱ ደቀ መዝሙር ስለ መሆን ለሰውዬው ለማስተማር በምሳሌ ይመልስለታል። ኢየሱስን ከመከተል ይልቅ ትኩረቱን ከእርሱ በፊት በነበሩ ሰዎች ላይ የሚያደርግ ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት ተስማሚ አይደለም ማለቱ ነው።

ማንም እጁን በማረሻ ላይ የሚያደርግ

እዚህ ጋ፣ “እጁን በ - የሚያደርግ” የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ሰውዬው አንድ ነገር ለማድረግ ይጀምራል ማለት ነው። አ.ት፡ “ማንም እርሻውን ለማረስ ጀምሮ” (የአነጋገር ዘይቤ እና የማይታወቁትን ተርጉማቸው የሚለውን ተመልከት)

ወደ ኋላው የሚመለከት

ማንም እያረሰ ወደ ኋላው የሚመለከት ማረሻውን መሄድ በሚገባው አቅጣጫ መምራት አይችልም። ያ ሰው በአግባቡ ለማረስ ወደ ፊት መመልከቱ ላይ ማተኮር አለበት።

ለእግዚአብሔር መንግሥት ብቁ

“ለእግዚአብሔር መንግሥት ጠቃሚ” ወይም “ለእግዚአብሔር መንግሥት ተስማሚ”