am_tn/luk/09/59.md

1.6 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ ከሰዎች ጋር መንገድ እየሄደ መናገሩን ቀጥሏል።

ተከተለኝ

ኢየሱስ ይህንን በማለት ሰውዬው የእርሱ ደቀ መዝሙር እንዲሆንና ከእርሱ ጋር እንዲሄድ እየጠየቀው ነው።

መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብረው ፍቀድልኝ

የሰውዬው አባት ስለ ሞተ ወዲያው ሊቀብር ወይስ አባቱ እስኪሞት ለረጅም ጊዜ ቆይቶ ከዚያ በኋላ ሊቀብረው እንዲችል ፈልጎ ይሆን ግልጽ አይደለም። ዋናው ነጥብ ሰውየው ኢየሱስን ከመከተሉ በፊት አስቀድሞ አንድ ነገር ማድረግ ይፈልጋል።

በመጀመሪያ እንድሄድ ፍቀድልኝ

“ያንን ከማድረጌ በፊት እንድሄድ ፍቀድልኝ”

ሙታን የራሳቸውን ሙታን እንዲቀብሩ ተዋቸው

ኢየሱስ በቀጥታ የሞቱ ሰዎች ሌሎች የሞቱ ሰዎችን ይቀብራሉ ማለቱ አይደለም። ሊሆኑ የሚችሉ “የሙታን” ትርጉሞች፣ 1) በቅርቡ የሚሞቱትን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው፣ ወይም 2) ኢየሱስን የማይከተሉትንና በመንፈስ የሞቱትን የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው የሚሉት ናቸው። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ሙታን

ይህ በጥቅሉ የሞቱትን ሰዎች ያመለክታል። አ.ት፡ “የሞቱ ሰዎች” (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ተመልከት)