am_tn/luk/09/51.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ መወሰኑ ግልጽ ሆነ።

የሚያርግበት ቀን በቀረበ ጊዜ

“የሚያርግበት ሰዓት በመጣ ጊዜ” ወይም “የሚያርግበት ሰዓት በደረሰ ጊዜ”

ፊቱን አቀና

የዚህ የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም “ቁርጥ ውሳኔ አደረገ” የሚል ነው። አ.ት፡ “አዕምሮውን አሠራው” ወይም “ወሰነ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ሁሉንም ነገር እንዲያዘጋጁለት

ይህ ማለት እርሱ ወደዚያ እንዲደርስ የመናገሪያ ስፍራን፣ ማደሪያ ቦታንና ምግብን ጨምሮ ዝግጅት ማድረግን ያካትታል።

አልተቀበሉትም

“በዚያ እንዲቆይ አልፈለጉም”

ፊቱን በኢየሩሳሌም አቅጣጫ አቅንቶ ስለነበረ

ሳምራውያንና አይሁድ እርስ በእርሳቸው ይጠላሉ ነበር። በመሆኑም ኢየሱስ ወደ አይሁድ ዋና ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም በሚያደርገው ጉዞ ሳምራውያን አልረዱትም።