am_tn/luk/09/49.md

1.3 KiB

ዮሐንስ መለሰ

“ዮሐንስ እንዲህ ሲል መለሰ” ወይም “ዮሐንስ ለኢየሱስ መለሰለት”። ኢየሱስ የሁሉ ታላቅ ስለ መሆን ለተናገረው ለዮሐንስ ምላሽ እየሰጠ ነበር። እርሱ የሰጠው ለጥያቄ መልስ አይደለም።

አይተናል

ኢየሱስ ሳይሆን ዮሐንስ ስለ ራሱ ይናገራል፣ ስለዚህ እዚህ ጋ “እኛ” አግላይ ነው። (አግላይና አካታች “እኛ” የሚለውን ተመልከት)

በስምህ

ይህ ማለት ሰውዬው በኢየሱስ ኃይልና ሥልጣን ሲናገር ነበር። (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አታስቁሙት

ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እንዲቀጥል ፍቀዱለት”

የማይቃወማችሁ ሁሉ የእናንተ ወገን ነው

አንዳንድ የዘመናችን ቋንቋዎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው አባባሎች አሏቸው። አ.ት፡ “አንድ ሰው እናንተን ከመሥራት ካላገዳችሁ እየረዳችሁ እንዳለ ያህል ነው” ወይም “አንድ ሰው እናንተን በመቃወም ካልሠራ ከእናንተ ጋር እየሠራ ነው”