am_tn/luk/09/43.md

2.1 KiB

ሁሉም በእግዚአብሔር ታላቅነት ተገረሙ

ኢየሱስ ተአምራትን አደረገ፣ ሆኖም ከፈውሱ ጀርባ የነበረው ኃይል እግዚአብሔር እንደሆነ ሕዝቡ ተገንዝቧል።

ሲያደርግ የነበረው ነገር ሁሉ

“ኢየሱስ ሲያደርግ የነበረው ነገር ሁሉ”

እነዚህ ቃላት በጆሮአችሁ ጠልቀው ይግቡ

ይህ የአነጋገር ዘይቤ ሲሆን ትኩረት መስጠት አለባቸው ማለት ነው። አ.ት፡ “በጥንቃቄ ስሙ፣ አስታውሱም” ወይም “ይህንን አትርሱ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተክዶ ይሰጣል

ይህ ከአድራጊ አንቀጽ ጋር ሊነገር ይችላል። እዚህ ጋ “እጅ” የሚያመለክተው ኃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው። አ.ት፡ “የሰውን ልጅ ይክዱታል፣ በሰዎች ቁጥጥር ስር እንዲሆንም ያደርጉታል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተክዶ ይሰጣል

ኢየሱስ በሦስተኛ መደብ የሚናገረው ስለ ራሱ ነው። “እጅ” የሚለው ቃል እጅ ያላቸውን ሰዎች ወይም በፈሊጣዊ አነጋገር እነዚያን እጆች የሚጠቀመውን ኃይል ገላጭ ነው። እነዚህ ሰዎች ማን እንደሆኑ ግልጽ ማድረግ ያስፈልግህ ይሆናል። አ.ት፡ “የሰው ልጅ የሆንኩ እኔ በሰዎች እጅ እካዳለሁ” ወይም “የሰው ልጅ ተክዶ ለጠላቶቹ ኃይል ይሰጣል” ወይም “የሰው ልጅ የሆንኩ እኔ ተክጄ ለጠላቶቼ ታልፌ እሰጣለሁ”

ከእነርሱ ተሰውሮ ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ትርጉሙን ከእነርሱ ሰወረው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)