am_tn/luk/09/41.md

1.3 KiB

ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ

“ኢየሱስ እንዲህ በማለት መለሰለት”

እናንተ እምነት የለሾችና ብልሹ ትውልድ

ኢየሱስ ይህንን የተናገረው ለደቀ መዛሙርቱ ሳይሆን ተሰብስቦ ለነበረው ሕዝብ ነው።

ብልሹ ትውልድ

“ምግባረ ብልሹ ትውልድ”

ከእናንተ ጋር የምሆነውና የምታገሳችሁ እስከ መቼ ነው?

እዚህ ጋ በእንግሊዝኛ “ዩ” የተባለው ብዙ ቁጥር ነው። ሰዎች ባለማመናቸው ኢየሱስ ሐዘኑን ለመግለጽ እነዚህን ጥያቄዎች ይጠይቃል። እንደ መግለጫ ሊጻፉ ይችላሉ። አ.ት፡ “ለረጅም ጊዜ ከእናንተ ጋር ነበርኩ፣ እናንተ ግን አታምኑም። እስከ መቼ ልታገሳችሁ ያስፈልገኝ እንደሆነ እደነቃለሁ” (Forms of You እና ምላሽ የማይፈልግ ጥያቄ የሚለውን ተመልከት)

ልጅህን ወደዚህ አምጣው

እዚህ ጋ የእንግሊዝኛው “የአንተን” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው። ኢየሱስ እየተናገረ ያለው በቀጥታ አስታውቆት ለነበረው ለአባትየው ነው።