am_tn/luk/09/37.md

1.2 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ከኢየሱስ አንጸባራቂ መገለጥ በኋላ በቀጣዩ ቀን ደቀ መዛሙርት ሊፈውሱት ያልቻሉትን በአጋንን ተይዞ የነበረውን ልጅ ይፈውሰዋል።

እነሆ፣ ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው

“እነሆ” የሚለው ቃል በታሪኩ ውስጥ ለተነገረው አዲስ ሰው ያነቃናል። የአንተ ቋንቋ ይህንን መግለጽ የሚያስችል መንገድ ይኖረው ይሆናል። እንግሊዝኛው “በሕዝቡ መካከል አንድ ሰው ነበረ” የሚለውን ይጠቀማል። (አዲስና ነባር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

አየኸው፣ መንፈስ

“አየኸው” የሚለው ቃል በሰውዬው ታሪክ ውስጥ ክፉዉን መንፈስ ያስተዋውቀናል። የአንተ ቋንቋ ይህንን መግለጽ የሚያስችል መንገድ ይኖረው ይሆናል። አ.ት፡ “ክፉ መንፈስ አለ” (አዲስና ነባር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

አረፋ ይደፍቃል

x