am_tn/luk/09/34.md

1.7 KiB

እርሱ ይህንን እየተናገረ እያለ

“እነዚህን ነገሮች ጴጥሮስ በመናገር ላይ እያለ”

ፈርተው ነበር

እነዚህ ጎልማሳ ደቀ መዛሙርት የፈሩት ደመናውን አልነበረም። ይህ ሐረግ የሚጠቁመው ከደመናው ጋር አንድ ያልተለመደ ዓይነት ፍርሃት እንደመጣባቸው ነው። አ.ት፡ “ደንግጠው ነበር”

ወደ ደመናው ውስጥ ገቡ

ደመናው ያደረገው ነገር ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ደመናው ከበባቸው”

ከደመናው ውስጥ ድምፅ መጣ

ድምፁ የእግዚአብሔር ብቻ እንደሚሆን ግልጽ ነው። አ.ት፡ “ከደመናው ውስጥ እግዚአብሔር ተናገራቸው”

ልጅ

ይህ ለእግዚአብሔር ልጅ፣ ለኢየሱስ አስፈላጊ የሆነ ማዕረግ ነው። (አባትና ልጅን መተርጎም የሚለውን ተመልከት)

የተመረጠው

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እኔ የመረጥኩት” ወይም “እኔ መርጬዋለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ያዩትን … ዝም አሉ

ይህ ከሁነቱ የተነሣ በራሱ በታሪኩ ውስጥ ከታሪኩ በኋላ ስለሆነው ነገር የሚናገር መረጃ ነው (የታሪኩ መጨረሻ የሚለውን ተመልከት)።

ዝም አሉ … ለማንም አልተናገሩም

የመጀመሪያው ሐረግ ወዲያው የሰጡትን ምላሻቸውን ሲያመለክት ሁለተኛው በቀጣዮቹ ቀናት ያደረጉትን ያመለክታል።