am_tn/luk/09/30.md

834 B

እነሆ

እዚህ ጋ፣ “እነሆ” የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚነገረው አስገራሚ መረጃ ትኩረት እንድንሰጥ ያነቃናል። አ.ት፡ “በድንገት”

በደማቅ ክብር ተገልጠው

ይህ ሐረግ ሙሴና ኤልያስ ምን ይመስሉ እንደነበሩ መረጃ ይሰጣል። አንዳንድ ቋንቋዎች እንደ ተናጠል አንቀጽ ሊተረጉሙት ይችላሉ። አ.ት፡ “በደማቅ ክብር ተገለጡ” ወይም “እጅግ ያንጸባርቁ ነበር”

ስለ እርሱ መሄድ

“ስለ እርሱ መለየት” ወይም “ኢየሱስ ይህንን ዓለም እንዴት እንደሚተው”። ይህ ስለ ሞቱ በትህትና የተነገረበት መንገድ ነበር። አ.ት፡ “ስለ ሞቱ”