am_tn/luk/09/20.md

2.0 KiB

ከዚያም እርሱ እንዲህ አላቸው

“ከዚያም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው”

ለአንድም ሰው እንዳትናገሩ አላቸው

“ለማንም እንዳይናገሩ” ወይም “ለማንም መናገር እንደሌለባቸው”። ይህ እንደ ቀጥተኛ ትዕምርተ ጥቅስ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ለማንም አትንገሩ” አላቸው። (ግልጽ የሆነና ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ተመልከት)

የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበል አለበት

“ሰዎች የሰውን ልጅ ታላቅ መከራ እንዲቀበል ያደርጉታል”

የሰው ልጅ … እርሱ ይነሣል

ኢየሱስ ወደ ራሱ እያመለከተ ነው። አ.ት፡ “የሰው ልጅ የሆንኩ እኔ … እኔ እነሣለሁ” (አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጸሐፊዎች ይጣላል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሽማግሌዎቹ፣ የካህናት አለቆችና ጸሐፊዎች ይጥሉታል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ይገደላል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ይገድሉታል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በሦስተኛው ቀን

“ከሞተ ከሦስት ቀን በኋላ” ወይም “በሞተ በሦስተኛው ቀን”

ይነሣል

“እንደገና በሕይወት እንዲኖር ይደረጋል”። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር እንደገና በሕይወት እንዲኖር ያደርገዋል” ወይም “እንደገና በሕይወት ይኖራል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)