am_tn/luk/09/18.md

1.4 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ብቻ በአጠገቡ ሆነው እየጸለየ ነው፣ ኢየሱስ ማን እንደሆነ መነጋገር ይጀምራሉ። ኢየሱስ በቅርቡ እንደሚሞትና እንደሚነሣ ይነግራቸዋል፣ ሊያደርጉት በጣም ከባድ ቢሆንም እንኳን እንዲከተሉት አጥብቆ ያሳስባቸዋል።

ከዚህ በኋላ

ይህ ሐረግ እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው የአዲስ ሁነት ጅማሬን ለማመልከት ነው። (አዲስ ሁነትን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

በግሉ ሲጸልይ

“ብቻውን ሲጸልይ”። ደቀ መዛሙርቱ ከኢየሱስ ጋር ነበሩ፣ ነገር ግን እርሱ በግሉና ለብቻው ይጸልይ ነበር።

አጥማቂው ዮሐንስ

እዚህ ጋ የጥያቄውን አካል እንደገና መናገር ሊጠቅም ይችላል። አ.ት፡ “አንዳንዶች አጥማቂው ዮሐንስ ነህ ይላሉ”

ጥንት ከነበሩት ነቢያት አንዱ ተነሥቷል

ይህ ምላሽ ከኢየሱስ ጥያቄ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ማብራራት ሊጠቅም ይችላል። አ.ት፡ “ጥንት ከነበሩት ነቢያት አንዱ ሆነህ ተነሥተሃል”

ተነሥቷል

“ወደ ሕይወት ተመልሷል”