am_tn/luk/09/07.md

1.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ ቁጥሮች ስለ ሔሮድስ መረጃ ለመስጠት ጣልቃ ይገባሉ።

በዚህ ጊዜ ሔሮድስ

ይህ ሐረግ በዋናው የታሪክ መስመር ላይ ቆም እንዲባል ምልክት ይሰጣል። እዚህ ጋ ሉቃስ ስለ ሔሮድስ ዳራዊ መረጃ ይናገራል። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)

የአራተኛው ክፍል ገዢ

ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን አንድ አራተኛ ይገዛ የነበረውን ሔሮድስ አንቲጳስን ነው።

ግራ ተጋባ

ተደናገረ፣ መረዳት አቃተው

በአንዳንዶች ተነግሮ ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አንዳንድ ሰዎች ተናግረዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ሌሎች ደግሞ ከጥንት ነቢያቶች አንዱ ተነሥቷል

“ተናግረዋል” የሚለውን ቃል ቀደም ብሎ ካለው ሐረግ መገንዘብ ይቻላል። አ.ት፡ “ሌሎች ደግሞ ከጥንት ነቢያቶች አንዱ ተነሥቷል አሉ”

የዮሐንስን ራስ ቆረጥሁት። ይህ ማነው?

ዮሐንስ ከሙታን ሊነሣ አይችልም ብሎ ገምቷል። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ራሱን ስለቆረጥኩት ዮሐንስ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ፣ ይህ ሰው ማነው?”

የዮሐንስን ራስ ቆረጥሁት

x