am_tn/luk/09/03.md

1.6 KiB

እንዲህ አላቸው

“ኢየሱስ ለአሥራ ሁለቱ እንዲህ አላቸው”። ይህ የሆነው ከመሄዳቸው በፊት መሆኑን መናገር ሊጠቅም ይችላል። አ.ት፡ “ከመሄዳቸው በፊት ኢየሱስ እንዲህ አላቸው”

ምንም ነገር አትውሰዱ

“ምንም ነገር ይዛችሁ አትሂዱ” ወይም “ምንም ነገር አታምጡ”

ለጉዞአችሁ

“ለመንገዳችሁ” ወይም “በምትጓዙበት ጊዜ”። ወደ ኢየሱስ እስኪመለሱ ድረስ ከመንደር ወደ መንደር በሚዘዋወሩበት ጊዜ ለጉዞአቸው ምንም ነገር መውሰድ አይኖርባቸውም።

በትር

ሰዎች ተራራ ሲወጡ ወይም ጎርበጥባጣ መንገድ ላይ ሲሄዱ ሚዛናቸውን ለመጠበቅ እንዲሁም አጥቂዎችን ለመከላከል የሚጠቀሙበት ረዘም ያለ ዘንግ ነው።

ሻንጣ

መንገደኛ ለጉዞው የሚፈልጋቸውን ነገሮች ለመያዣነት የሚጠቀምበት ቦርሳ

እንጀራ

እዚህ ጋ፣ ይህ ጥቅም ላይ የዋለው በጥቅሉ “ምግብ”ን ለማመልከት ነው።

ወደ የትኛውም ወደምትገቡበት ቤት

“ወደምትገቡበት ወደ ማናቸውም ቤት”

በዚያ ቆዩ

“በዚያ ሰንብቱ” ወይም “በዚያ ቤት ውስጥ ለጊዜው በአንግድነት ኑሩ”

ከዚያ እስክትሄዱ ድረስ

“ያንን ከተማ ለቃችሁ እስክትሄዱ ድረስ” ወይም “ያንን ስፍራ እስክትለቁ ድረስ”