am_tn/luk/08/51.md

1.2 KiB

ወደ ቤት በመጣ ጊዜ

“ወደ ቤት በመጡ ጊዜ”። ኢየሱስ ከኢያኢሮስ ጋር ወደዚያ ሄደ። ደግሞም አንዳንድ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ከእነርሱ ጋር ሄዱ።

ከጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ ከልጅቱ አባትና እናት በስተቀር … ለማንም አልፈቀደም

ይህ በአዎንታዊነት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ኢየሱስ ለጴጥሮስ፣ ለዮሐንስ፣ ለያዕቆብ፣ ለልጅቱ አባትና እናት ብቻ ከእርሱ ጋር ወደ ውስጥ እንዲገቡ ፈቀደላቸው”

የልጅቱ አባት

ይህ የሚያመለክተው ኢያኢሮስን ነው።

ሁሉም ያለቅሱና ሙሾ ያወጡላት ነበር

ይህ በዚያ ባህል የተለመደ የሐዘን መግለጫ መንገድ ነበር። አ.ት፡ “በዚያ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ልጅቱ ሞታ ስለነበር ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በማልቀስ ምን ያህል እንዳዘኑ በመግለጽ ላይ ነበሩ”

መሞቷን ስላወቁ ሳቁበት

“ልጅቱ መሞቷን ስላወቁ ሳቁበት”