am_tn/luk/08/45.md

1.0 KiB

ብዙ ሕዝብ … እያጋፉህ ነው

ጴጥሮስ ይህንን ሲል የትኛውም ሰው ኢየሱስን ሊነካው ይችል እንደነበር ማመልከቱ ነው። አስፈላጊ ከሆነ ይህ ግልጽ ያልሆነ መረጃ ግልጽ ሊደረግ ይችላል። አ.ት፡ “በዙሪያህ ብዙ ሕዝብ ከቦ እያጋፋህ ነው፣ ስለዚህ ከእነርሱ አንዱ ነክቶህ ይሆናል”

አንድ ሰው ነክቶኛል

ይህንን ሆነ ተብሎ የተደረገውን “መንካት” ከሕዝቡ ድንገተኛ መንካት መለየት ሊጠቅም ይችላል። አ.ት፡ “አንድ ሰው ሥራዬ ብሎ ነክቶኛል”

ከእኔ ኃይል እንደ ወጣ አውቃለሁ

ኢየሱስ ኃይል አላጣም ወይም አልደከመም፣ ነገር ግን የእርሱ ኃይል ሴቲቱን ፈውሷታል። አ.ት፡ “የሚፈውስ ኃይል ከእኔ እንደወጣ አውቃለሁ” ወይም “ኃይሌ አንድ ሰው እንደ ፈወሰ ተሰምቶኛል”