am_tn/luk/08/43.md

1.2 KiB

በዚያ አንዲት ሴት ነበረች

ይህ በታሪኩ ውስጥ አንድ አዲስ ገጸ ባህርይ ያስተዋውቃል። (አዲስና ነባር ተሳታፊዎችን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

ትደማ የነበረች

“ደም ይፈሳት የነበረች”። ተገቢው ጊዜ ባይሆንም እንኳን ምናልባት በማህፀን እያለች ጀምሮ ሳትደማ አልቀረችም። አንዳንድ ባህሎች እንደዚህ ያለውን ሁኔታ በትህትና የሚያመላክቱበት መንገድ ይኖራቸዋል።

በማንም ልትፈወስ አልቻለችም

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ነገር ግን ማንም ሊፈውሳት አልቻለም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የልብሱን ጫፍ ነካች

“የመጎናጸፊያውን ዘርፍ ነካች”። አይሁዳውያን ወንዶች በእግዚአብሔር ሕግ እንደታዘዘው የክብረ በዓል ልብሶቻቸው አካል በማድረግ በመጎናጸፊያዎቻቸው ላይ መነሳንስ ይደርቡ ነበር። እርሷ የነካችው ይህንን ሊሆን ይችላል።