am_tn/luk/08/40.md

1.7 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከሐይቁ በሌላኛው በኩል ከገሊላ በተመለሱ ጊዜ 12 ዓመት የሆናትን የምኩራብ አለቃውን ልጅ፣ እንዲሁም 12 ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረችውን ሴት ፈወሳቸው።

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ ቁጥሮች ስለ ኢያኢሮስ ዳራዊ መረጃ ይሰጣሉ። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)

ሕዝቡ ተቀበለው

“ሕዝቡ በደስታ ሰላምታ ሰጡት”

ከምኩራብ አለቆች አንዱ

“በአካባቢው በነበረ ምኩራብ አለቆች ከሆኑት አንዱ” ወይም “በዚያች ከተማ በምኩራብ የተገናኘው የሕዝቡ መሪ”

በኢየሱስ እግር ላይ ተደፋ

ሊሆኑ የሚችሉት ትርጉሞች፣ 1) “በኢየሱስ እግር ስር ሰገደ” ወይም 2) “በኢየሱስ እግር አጠገብ በምድር ላይ ወደቀ”። ኢያኢሮስስ የወደቀው በድንገት አይደለም። ይህንን ያደረገው ለኢየሱስ ስላለው ትህትና እና አክብሮት ምልክት እንዲሆን ነው የሚሉት ናቸው።

እየሞተች ነው

“ልትሞት ነው”

ኢየሱስ በመንገድ ላይ እያለ

አንዳንድ ተርጓሚዎች ኢየሱስ ከኢያኢሮስ ጋር ለመሄድ መስማማቱን በቅድሚያ መናገር ይኖርባቸዋል። አ.ት፡ “ስለዚህ ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ለመሄድ ተስማማ። በመንገድ ላይ እያለ”

ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ሆነው አጋፉት

“ሰዎቹ በኢየሱስ ዙሪያ ተጠጋግተው ከበውት ነበር”