am_tn/luk/08/28.md

1.5 KiB

ኢየሱስን ባየው ጊዜ

“አጋንንት የነበሩበት ሰው ኢየሱስን ባየው ጊዜ”

ጮኸ

“በታላቅ ድምፅ ጮኸ” ወይም “በስቃይ ጮኸ”

በፊቱ ወደቀ

“በኢየሱስ ፊት በምድር ላይ ወደቀ”። የወደቀው በድንገት አይደለም።

በታላቅ ድምፅ ተናገረ

“በጩኸት ተናገረ” ወይም “ከፍ ባለ ድምፅ ጮኸ”

ከእኔ ጋር ምን ጉዳይ አለህ

የዚህ የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም “ለምን ታስቸግረኛለህ?” ማለት ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የልዑል እግዚአብሔር ልጅ

ይህ ለኢየሱስ አስፈላጊ ማዕረግ ነው። (አባትን እና ልጅን መተርጎም የሚለውን ተመልከት)

ከያዘው ብዙ ጊዜ ሆኖት ነበር

“ሰውየውን ከተቆጣጠረው ብዙ ጊዜ ሆኖት ነበር” ወይም “ወደ እርሱ ከገባበት ብዙ ጊዜ ሆኖት ነበር”። ይህ የሚናገረው ኢየሱስ ከሰውዬው ጋር ከመገናኘቱ በፊት አጋንንቱ ብዙ ጊዜ ያደርገው የነበረውን ነው።

ቢታሰርም እንኳን … ይጠብቁት ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች በሰንሰለትና በእግር ብረት ቢያስሩትና ቢጠብቁትም እንኳን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)