am_tn/luk/08/26.md

1.5 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ ከአንድ ሰው ብዙ አጋንንት ወዳወጣበት ወደ ጌርጌሴኖን ባህር ዳርቻ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር መጣ።

ጌርጌሴኖን ወደሚባል ሀገር

ጌርጌሶናዊያን ጌርጌሴኖን የምትባል ከተማ ሰዎች ነበሩ። (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ከገሊላ ሐይቅ ማዶ

“ከገሊላ ሐይቅ በወዲያኛው ማዶ”

አንድ ሰው ከከተማው

“አንድ ሰው ከጌርጌሴኖን ከተማ”

አጋንንት የነበሩበት አንድ ሰው ከከተማ

ሰውየው አጋንንት ነበሩበት፤ አጋንንት የኖሩት በከተማው ላይ አልነበረም። አ.ት፡ “አንድ ሰው ከከተማ. . . ይህ ሰው አጋንንት ነበሩበት”

አጋንንት የነበሩበት

“አጋንንት ተቆጣጥረውት የነበረ” ወይም “አጋንንት የተቆጣጠሩት”

ለረጅም ጊዜ ራቁቱን ይኖር ነበር … ነገር ግን በመቃብር መካከል

ይህ አጋንንት ስለነበሩበት ሰው ዳራዊ መረጃ ነው። (ዳራዊ መረጃ የሚለውን ተመልከት)

ራቁቱን ይኖር ነበር

“ልብስ አይለብስም ነበር”

መቃብር

ይህ ሰዎች ሬሳ የሚያኖሩበት፣ ምናልባት አንድ ሰው ለመጠለያነት የሚጠቀምበት ዋሻ ወይም አነስተኛ ግንብ ሊሆን ይችላል።