am_tn/luk/08/22.md

1.2 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የጌንሳሬጥን ሐይቅ ለመሻገር በጀልባ ይጠቀማሉ። ደቀ መዛሙርቱ በሚነሣው ማዕበል አማካይነት ስለ ኢየሱስ ኃይል በይበልጥ ይማራሉ።

ሐይቁ

ይህ የጌንሳሬጥ ሐይቅ ነው፣ የገሊላ ባህር ተብሎም ይጠራል።

መጓዝ ጀመሩ

የዚህ አገላለጽ ትርጉም፣ ሐይቁን ለመሻገር በጀልባቸው መጓዝ ጀመሩ የሚል ነው።

በመጓዝ ላይ እያሉ

“ሲሄዱ ሳሉ”

አንቀላፋ

“ማንቀላፋት ጀመረ”

ከባድ ዐውሎ ንፋስ ወረደ

“በጣም ታላቅ የሆነ ዐውሎ ንፋስ ጀመረ” ወይም “በጣም ኃይለኛ ንፋስ በድንገት መንፈስ ጀመረ”

ጀልባቸው በውሃ ይሞላ ነበር

ኃይለኛው ንፋስ ብርቱ ሞገድ በማስነሣት የጀልባዋን ጎንና ጎን በውሃ እንዲገፋት አደረገ። ይህ በግልጽ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ንፋሱ ከፍተኛ ሞገድ በመፍጠር ጀልባቸውን በውሃ መሙላት ጀመረ”