am_tn/luk/08/16.md

2.4 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ በሌላ ምሳሌ መናገሩን ይቀጥላል፣ ከዚያም ቤተሰቦቹ በእርሱ ሥራ ውስጥ ስለሚኖራቸው ሚና አጽንዖት በመስጠት ለደቀ መዛሙርቱ መናገሩን ያበቃል።

ማንም የለም

ይህ ሌላ ምሳሌ የመጀመሩ ምልክት ነው። (ምሳሌዎች የሚለውን ተመልከት)

ተደብቆ ሳይታወቅ የሚቀር ምንም ነገር የለም

ይህ ድርብ አሉታ እንደ አዎንታዊ ንግግር ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “የተደበቀ ነገር ሁሉ እንዲታወቅ ይደረጋል” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)

የማይታወቅና ወደ ብርሃን የማይመጣ ምስጢር ሆኖ የሚቀር ምንም ነገር የለም

ይህ ድርብ አሉታ እንደ አዎንታዊ ንግግር ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “ምስጢር የሆነው ነገር ሁሉ ወደ ብርሃን ይመጣል፣ እንዲታወቅም ይደረጋል” (ድርብ አሉታ የሚለውን ተመልከት)

ላለው የበለጠ ይሰጠዋል

ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ስለ ማስተዋልና ስለ ማመን መሆኑን ከዐውዱ በግልጽ መረዳት ይቻላል። ይህ በግልጽ ሊነገርና ወደ አድራጊ ድምፅ ሊቀየር ይችላል። አ.ት፡ “ማስተዋል ላለው ለማንም ቢሆን የበለጠ ማስተዋል ይሰጠዋል” ወይም “እግዚአብሔር እውነትን የሚያምኑትን እነዚያን የበለጠ እንዲያስተውሉ ደግሞ ያስችላቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ከሌለው … ከእርሱ ይወሰድበታል

ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ስለ ማስተዋልና ስለ ማመን መሆኑን ከዐውዱ በግልጽ መረዳት ይቻላል። ይህ በግልጽ ሊነገርና ወደ አድራጊ ድምፅ ሊቀየር ይችላል። አ.ት፡ “ማንም ማስተዋል የሌለው ሰው አለኝ የሚለውን ማስተዋል እንኳን ያጣዋል” ወይም “ነገር ግን እውነትን የማያምኑትን እነዚያን ተረድተነዋል የሚሉትን ጥቂቱን ማስተዋል እንኳን እንዳያስተውሉ ያደርጋቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)