am_tn/luk/08/14.md

2.8 KiB

በእሾህ መካከል የወደቀው ዘር ሰዎች ናቸው

“በእሾህ መካከል የወደቀው ዘር ሰዎችን ይወክላል” ወይም “በምሳሌው ውስጥ በእሾህ መካከል የወደቀው ዘር ሰዎችን ይወካላል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

የዚህ ሕይወት ምቾት … ታንቀዋል

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የዚህ ሕይወት ፍላጎት፣ ባለጸግነትና ደስታ ያንቃቸዋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ፍላጎት

ሰዎች የሚጨነቁላቸው ነገሮች

የዚህ ሕይወት ደስታ

“በዚህ ሕይወት ሰዎች የሚደሰቱባቸው ነገሮች”

በዚህ ሕይወት ፍላጎት፣ ባለጸግነትና ደስታ ስለ ታነቁ በተገቢው ሁኔታ አያፈሩም

ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር የሚያመለክተው አረሙ የቡቃያውን ብርሃንና ማዕድናት በማቋረጥ ከዕድገት እንደሚገታቸው ነው። አ.ት፡ “አረም መልካሙን ቡቃያ ከማደግ እንደሚገታው የዚህ ሕይወት ፍላጎት፣ ብልጽግና እና ደስታም እነዚህን ሰዎች ፍሬአማ ከመሆን ይገታቸዋል” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ፍሬአቸው አይበስልም

“የደረሰ ፍሬ አያፈሩም”። ብስል ፍሬ የመልካም ሥራ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “የበሰለ ፍሬ እንደማያፈራ ተክል እነርሱም መልካም ሥራ አይሠሩም” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

በመልካሙ መሬት ላይ የወደቀው ዘር እነዚህ ናቸው

“በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር ሰዎችን ይወክላል” ወይም “በምሳሌው ውስጥ በመልካም መሬት ላይ የወደቀው ዘር ሰዎችን ይወክላል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ቃሉን ሰምተው

“መልዕክቱን ሰምተው”

በመልካምና ቅን ልብ

እዚህ ጋ “ልብ” የሰውን አሳብ ወይም ፍላጎት የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በመልካምና ቅን ምኞት”

በትዕግስት በመጽናት ፍሬ የሚያፈራ

“በትዕግስት በመጽናት ፍሬ የሚሰጡ” ወይም “በማያቋርጥ ጥረት ፍሬ የሚሰጡ”። ፍሬ የመልካም ሥራ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “መልካም ፍሬ እንደሚያፈራ ጤነኛ ተክል በመጽናት መልካም ሥራን ይሠራሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)