am_tn/luk/08/11.md

3.1 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ ስለ መሬት የተናገረውን ምሳሌ ትርጉም ለደቀ መዛሙርቱ ማብራራት ይጀምራል።

ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው

“ዘሩ ከእግዚአብሔር የመጣው መልዕክት ነው”

በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚያ

“በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር እርሱ”። ኢየሱስ ከሰዎች ጋር በማገናኘት ዘሩ ምን እንደሚሆን ይናገራል። አ.ት፡ “በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር ሰዎችን ይወክላል” ወይም “በምሳሌው ውስጥ በመንገድ ዳር የወደቀው ዘር ሰዎችን ይወክላል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

እነዚያ ናቸው

ዘሩ ሰው የሆነ ይመስል ኢየሱስ ስለ ሰዎች አንድ ነገር ለማሳየት በመፈለግ ስለ ዘር ይናገራል። አ.ት፡ “ሰዎች ላይ የሚሆነውን ያሳያል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዲያብሎስ ይመጣና ከልባቸው ቃሉን ይወስደዋል

እዚህ ጋ “ልባቸው” የሰዎችን አዕምሮ ወይም ውስጣዊ ማንነት የሚያመለክት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “ዲያብሎስ ይመጣና የእግዚአብሔርን መልዕክት ከውስጠኛው አስተሳሰባቸው ይወስደዋል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ይወስደዋል

ይህ ዘሩን የሚለቅም ወፍ በምሳሌው ውስጥ ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። ይህንን ስዕል ማሳየት የሚችልን ቃል በቋንቋህ ለመጠቀም ሞክር። (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

አምነው እንዳይድኑ

ይህ የዲያብሎስ ዓላማ እስከ ሆነ ድረስ እንደሚከተለው ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “ዲያብሎስ፣ ‘አምነው መዳን የለባቸውም’ ብሎ ስለሚያስብ” ወይም “እንዳያምኑና እግዚአብሔር እንዳያድናቸው” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በዐለት ላይ የወደቁት እነዚያ

“በዐለታማ አፈር ላይ የወደቁት እነዚያ”። ኢየሱስ ከሰዎች ጋር በማገናኘት ዘሩ ምን እንደሚሆን ይናገራል። አ.ት፡ “በዐለታማው መሬት ላይ የወደቀው ዘር ሰዎችን ይወክላል” ወይም “በምሳሌው ውስጥ በዐለታማው መሬት ላይ የወደቀው ዘር ሰዎችን ይወክላል” (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ዐለቱ

“ዐለታማው መሬት”

በፈተና ጊዜ

“መከራ በሚገጥማቸው ጊዜ”

ይወድቃሉ

የአነጋገር ዘይቤው ትርጉም “ማመናቸውን ያቆማሉ” ወይም “ኢየሱስን መከተላቸውን ያቆማሉ” የሚል ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)