am_tn/luk/08/09.md

1.7 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ መናገር ይጀምራል።

የ … እውቀት እግዚአብሔር የሰጣችሁን

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “የ… እውቀት እግዚአብሔር ሰጥቷችኋል” ወይም “የእግዚአብሔርን … መረዳት እንድትችሉ እግዚአብሔር አድርጓችኋል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የእግዚአብሔርን መንግሥት ምስጢር

እነዚህ የተደበቁ እውነቶች ናቸው፣ አሁን ግን ኢየሱስ ገልጧቸዋል።

ለሌሎች

“ለሌሎች ሰዎች”። ይህ የሚያመለክተው የኢየሱስን ትምህርት ያልተቀበሉትንና እርሱን ያልተከተሉትን ሰዎች ነው።

እያዩ እንዳያዩ

“ቢያዩም አይገነዘቡም”። ይህ ከነቢዩ ከኢሳይያስ የተጠቀሰ ጥቅስ ነው። አንዳንድ ቋንቋዎች የግሱን ባለቤት ማስታወቅ ያስፈልጋቸው ይሆናል። አ.ት፡ “ነገሮችን ቢያዩም አያስተውሏቸውም” ወይም “የሚሆኑትን ነገሮች ቢያዩም ምን ትርጉም እንዳላቸው አያስተውሉም”

እየሰሙ አያስተውሉም

“ቢሰሙም አያስተውሉም”። ይህ ከነቢዩ ከኢሳይያስ የተጠቀሰ ጥቅስ ነው። አንዳንድ ቋንቋዎች የግሱን ባለቤት ማስታወቅ ያስፈልጋቸው ይሆናል። አ.ት፡ “ትምህርትን ቢሰሙም እውነቱን አያስተውሉም”