am_tn/luk/08/01.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ ቁጥሮች ኢየሱስ በጉዞ ላይ እያለ ስለ ሰበከው ስብከት ዳራዊ መረጃ ይሰጣሉ።

እንዲህ ሆነ

ይህ ሐረግ እዚህ ጋ ጥቅም ላይ የዋለው የታሪኩን አዲስ ክፍል ለማመልከት ነው። (አዲስ ሁነትን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

ከክፉ መናፍስትና ከበሽታ ተፈውሰው የነበሩት

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ኢየሱስ ከክፉ መናፍስት ነጻ ያወጣቸውና ከበሽታ ፈውሷቸው የነበሩ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ማርያም … ሶስና

ሦስቱ ሴቶች ተጠቅሰዋል፡ ማርያም፣ ዮሐና፣ እና ሶስና (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የተባለችው ማርያም

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎች መግደላዊት ብለው የሚጠሯት ማርያም … ኢየሱስ ሰባት አጋንንት አስወጥቶላት የነበረች” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

የሔሮድስ ቤት ኃላፊ የሆነው የኩዛ ሚስት ዮሐና

ዮሐና የኩዛ ሚስት ስትሆን ኩዛ ደግሞ የሔሮድስ ቤት ኃላፊ ነበር። “የሔሮድስ ቤት ኃላፊ የሆነው የኩዛ ሚስት ዮሐና” (ስሞች እንዴት እንደሚተረጎሙ የሚለውን ተመልከት)

የሚያስፈልጋቸውን ያቀርቡ ነበር

“ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን በገንዘብ ይደግፉ ነበር”