am_tn/luk/07/48.md

1.5 KiB

ከዚያም እንዲህ አላት

“ከዚያም ሴቲቱን እንዲህ አላት”

ኃጢአትሽ ይቅር ተብሎልሻል

“ይቅር ተብለሻል”። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ኃጢአትሽን ይቅር ብዬሻለሁ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በአንድነት ጋደም ብለው

“በማዕዱ ዙሪያ በአንድነት ጋደም ብለው” ወይም “በአንድነት ሲመገቡ”

ኃጢአትን እንኳን ይቅር የሚል ይህ ማነው?

የሃይማኖት መሪዎች ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ያውቃሉ፣ ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደነበረ ግን አላመኑም። ይህ ጥያቄ ምናልባት ወቀሳ እንዲሆን ሳይታሰብ አልቀረም። አ.ት፡ “ይህ ሰው ማን እንደሆነ ነው የሚያስበው? ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው!” ወይም “ይህ ሰው እርሱ ብቻ ኃጢአትን ይቅር ለማለት የሚችለውን እግዚአብሔርን ለመሆን የሚሞክረው ለምንድነው?”

እምነትሽ አድኖሻል

“በእምነትሽ ምክንያት ድነሻል”። የነገር ስም የሆነው “እምነት” እንደ ድርጊት ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ስላመንሽ ድነሻል” (የነገር ስም የሚለውን ተመልከት)