am_tn/luk/07/33.md

2.6 KiB
Raw Permalink Blame History

እንጀራ አልበላም

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፣ 1) “አዘውትሮ መጾም” ወይም 2) “የተለመደውን ምግብ አለመብላት” የሚሉት ናቸው።

‘አጋንንት አለበት’ ትላላችሁ

ኢየሱስ የሚጠቅሰው ሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ይናገሩ የነበሩትን ነው። ይህ ያለ ቀጥተኛ ትዕምርተ ጥቅስ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “አጋንንት አለበት ትላላችሁ” ወይም “አጋንንት እንዳለበት አድርጋችሁ ትከሱታላችሁ” (ግልጽ የሆነና ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ተመልከት)

የሰው ልጅ

ኢየሱስ ወደ ራሱ ማመልከቱን ሕዝቡ እንደሚረዱ ጠብቋል። አ.ት፡ “የሰው ልጅ የሆንኩ እኔ” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

‘እነሆ፣ ከኃጢአተኞች … ሆዳምና ሰካራም ሰው ነው! ትላላችሁ

ይህ ቀጥተኛ እንዳልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ተደርጎ ሊተረጎም ይችላል። አ.ት፡ “እርሱ ከኃጢአተኞች … ሆዳምና ሰካራም ሰው ነው ትላላችሁ” ወይም “ከኃጢአተኞች… በመብላቱና ብዙ በመጠጣቱ ምክንያት ትከሱታላችሁ” (ግልጽ የሆነና ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ተመልከት)

‘ተመልከቱ፣ ከኃጢአተኞች … ሆዳምና ሰካራም ሰው ነው! ትላላችሁ

“የሰው ልጅ” የሚለውን “የሰው ልጅ የሆንኩ እኔ” ብለህ ተርጉመህ ከሆነ አንደኛ መደብን በመጠቀም ቀጥተኛ እንዳልሆነ መግለጫ አድርገህ መናገር ትችላለህ። አ.ት፡ “ከኃጢአተኞች… ሆዳምና ሰካራም እንደሆንኩ ትናገራላችሁ” (ቀጥተኛ የሆነና ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ እና አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

ሆዳም ሰው ነው

“ንፉግ በላተኛ ነው” ወይም “ባለማቋረጥ ብዙ ምግብ ይበላል”

ሰካራም

“ጠጪ” ወይም “ባለማቋረጥ የሚያሰክር መጠጥ አብዝቶ ይጠጣል”

ጥበብ በልጆቿ ሁሉ ጸድቃለች

ይህ ምናልባት ጥበበኞች ሰዎች ሕዝቡ ኢየሱስንና ዮሐንስን መቃወም እንዳልነበረባቸው የሚገነዘቡ መሆናቸውን ለማስተማር ኢየሱስ ከሁኔታው ጋር ያዛመደው ምሳሌአዊ አነጋገር ይሆናል።