am_tn/luk/07/29.md

1.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ

የዚህ መጽሐፍ ደራሲ የሆነው ሉቃስ ሰዎች ለዮሐንስና ለኢየሱስ ስላሳዩት ምላሽ አስተያየቱን ይሰጣል።

ሕዝቡ ሁሉ … ጊዜ የዮሐንስ ጥምቀት

ለበለጠ ግልጽነት የዚህ ቁጥር ቅደም ተከተል ሊስተካከል ይችላል። አ.ት፡ “ቀረጥ ሰብሳቢዎቹን ጨምሮ በዮሐንስ የተጠመቁ ሰዎች ሁሉ ይህንን በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔር ጻድቅ መሆኑን መሰከሩ”

እግዚአብሔር ጻድቅ መሆኑን መሰከሩ

“እግዚአብሔር ጻድቅ መሆኑን አሳይቷል አሉ” ወይም “እግዚአብሔር በጽድቅ አድርጓል ብለው መሰከሩ”

በዮሐንስ ጥምቀት ተጠምቀው ነበርና

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ዮሐንስ እንዲያጠምቃቸው ፈቅደው ነበርና” ወይም “ዮሐንስ አጥምቋቸው ነበርና” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን ዓላማ አልተቀበሉም

“እግዚአብሔር እንዲያደርጉ የፈለገባቸውን አልተቀበሉም” ወይም “እግዚአብሔር የነገራቸውን ላለመታዘዝ መረጡ”

በዮሐንስ አልተጠመቁም ነበር

ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ዮሐንስ እንዲያጠምቃቸው አልፈቀዱም ነበር” ወይም “የዮሐንስን ጥምቀት አልተቀበሉም” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)