am_tn/luk/07/27.md

2.1 KiB

ስለ እርሱ የተጻፈለት ይህ ነው

“ነቢያት ስለ እርሱ የጻፉለት ነቢይ እርሱ ነው” ወይም “ከረጅም ዓመታት በፊት ነቢያት የጻፉለት ሰው ዮሐንስ ነው”

እነሆ፣ እልካለሁ

በዚህ ቁጥር ኢየሱስ ከትንቢተ ሚልክያስን በመጥቀስ፣ ሚልክያስ የተናገረለት መልዕክተኛ ዮሐንስ መሆኑን ይናገራል።

በፊትህ

የዚህ የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም፣ “በፊት ለፊትህ” ወይም “ከአንተ ቀድሞ እንዲሄድ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የአንተ

በትዕምርተ ጥቅሱ ውስጥ እግዚአብሔር የሚናገረው ለመሲሑ ስለ ነበረ “የአንተ” የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ነው።

እልሃለሁ

ኢየሱስ የሚናገረው ለሕዝቡ ስለሆነ “አንተ” የሚለው ቃል ብዙ ቁጥርን አመልካች ነው። ኢየሱስ ይህንን የሚለው ቀጥሎ ለሚናገረው አስገራሚ እውነት አጽንዖት ለመስጠት ነው።

ከሴቶች በተወለዱት መካከል

“ሴቶች ከወለዷቸው መካከል”። ይህ ሰዎችን ሁሉ የሚያመለክት ዘይቤአዊ አነጋገር ነው። አ.ት፡ “በሕይወት ከነበሩት ሰዎች ሁሉ” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከዮሐንስ የሚበልጥ የለም

“የሚበልጠው ዮሐንስ ነው”

በእግዚአብሔር መንግሥት ታናሽ የሆነው

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር በሚመሠርተው መንግሥት ውስጥ አባል የሚሆነውን ማንኛውንም ሰው ነው።

እርሱን የሚበልጠው ይሆናል

በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ የሰዎች መንፈሳዊ ሁኔታ መንግሥቱ ከመመሥረቱ በፊት ከነበራቸው የሚበልጥ ይሆናል። አ.ት፡ “የመንፈሳዊ ሕይወታቸው ደረጃ ከዮሐንስ ይልቅ ከፍ ያለ ይሆናል”