am_tn/luk/07/18.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

አያያዥ መግለጫ፡

ዮሐንስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ኢየሱስን እንዲጠይቁት ይልካቸዋል።

የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለእነዚህ ነገሮች ሁሉ ነገሩት

ይህ በታሪኩ ውስጥ ስላለው አዲስ ሁነት ያስተዋውቃል። (አዲስ ሁነትን ማስተዋወቅ የሚለውን ተመልከት)

ነገሩት

“ለዮሐንስ ነገሩት”

እነዚህን ነገሮች ሁሉ

“ኢየሱስ ሲያደርጋቸው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ”

ሰዎቹ፣ “አጥማቂው ዮሐንስ . . . አንተ ነህ ወይስ ሌላውን እንጠብቅ? ብለን እንድንጠይቅህ ወደ አንተ ልኮናል” አሉት።

ይህ ዐረፍተ ነገር፣ አንድ ግልጽ የሆነ ትዕምርተ ጥቅስ እንዲኖረው እንደገና ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “ሰዎቹ ‘እየመጣህ ያለኸው አንተ ነህ? ወይስ ሌላ እንጠብቅ’ ብለው እንዲጠይቁት አጥማቂው ዮሐንስ የላካቸው መሆኑን ተናገሩ” ወይም “ሰዎቹ፣ ‘እየመጣህ ያለኸው አንተ ትሆን እንደሆን ወይም ሌላ መጠበቅ ይኖርብን እንደሆን እንድንጠይቅህ አጥማቂው ዮሐንስ ወደ አንተ ልኮናል’ አሉት”። (ግልጽ የሆነና ያልሆነ ትዕምርተ ጥቅስ ተመልከት)

ሌላ መጠበቅ ይኖርብን ይሆን?

“ሌላ እንጠብቅ?” ወይም “ሌላን ሰው እንጠባበቅ?”