am_tn/luk/07/16.md

1.7 KiB

አያያዥ መግለጫ፡

ይህ ኢየሱስ ሞቶ የነበረውን ሰው በመፈወሱ ምክንያት የሆነውን ነገር ይነግረናል።

በሁሉም ላይ ፍርሐት ወደቀባቸው

“ሁሉም ፍርሐት ሞላባቸው”። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሁሉም በጣም ፈሩ” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

በመካከላችን ታላቅ ነቢይ ተነሥቷል

ያመለክቱ የነበሩት ወደ አንድ ማንነቱ ወዳልታወቀ ነቢይ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ ነበር። እዚህ ጋ “ተነሥቷል” የሚለው ቃል “እንዲሆን ተደርጓል” ለሚለው የአነጋገር ዘይቤ ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “እግዚአብሔር ከእኛ አንዱን ታላቅ ነቢይ አድርጎታል” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ እና የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ጎብኝቷል

የዚህ የአነጋገር ዘይቤ ትርጉም “አስቧቸዋል” የሚል ነው። (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

ስለ ኢየሱስ የሆነው ይህ ወሬ ተስፋፋ

“ይህ ወሬ” የሚያመለክተው ሕዝቡ በቁጥር 16 ላይ ይናገሩት የነበሩትን ነገር ነው። ይህ በአድራጊ ድምፅ ሊነገር ይችላል። አ.ት፡ “ሕዝቡ ይህንን የኢየሱስን ዝና አሰራጩት” ወይም “ሕዝቡ የኢየሱስን ዝና ለሌሎች ነገሯቸው”

ይህ ወሬ

“ይህ ዝና” ወይም “ይህ መልዕክት”