am_tn/luk/06/49.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፦

ኢየሱስ እርሱ የሚናገረውን ሰምቶ የማይታዘዘውን ሰው ቤቱን ያለመሰረት ሰርቶ ጎርፍ በመጣ ጊዜ ቤቱ ከሚፈርስበት ሰው ጋር አነጻጽሮ ያቀርባል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰውየው ግን

“ግን” የሚለው ቃል ቀድሞ ከተነገረው ቤቱን መሰረት ላይ ከሰራው ሰው ጋር ጠንካራ የተቃራኒ ንጽጽር መኖሩን ያሳያል፡፡

ያለ መሰረት በመሬት ላይ

አንዳንድ ሰዎች መሰረት ያለው ቤት ጠንካራ እንደሆነ ላያውቁ ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን ቤቱን ከመስራት በፊት መሬትን ቆፍሮ መሰረትን አልገነባም ነበር” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መሰረት

ቤቱን ከመሬት ጋር የሚያገናኘው የሕንጻው ክፍል፡፡ ኢየሱስ በኖረበት ጊዜ የነበሩ ሰዎች መሬቱን አለት ድንጋይ እስከሚያገኙ ድረስ ቆፍረው በአለቱ ላይ ነበር ቤቱን ይገነቡ የነበረው፡፡ አለቱ የቤቱ መሰረት ነበር፡፡