am_tn/luk/06/45.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ፦

እዚህ ላይ ኢየሱስ የአንድ ሰውን ሃሳብ ሰውየው ካለው ከመልካም ወይም ከክፉ መዝገብ ጋር አነጻጽሮ ያቀርባል፡፡ መልካም ሰው መልካም ሃሳቦችን ሲያስብ መልካም ድርጊቶችን በመፈጸም ይጠመዳል፡፡ ክፉ ሰው ክፉ ሃሳቦችን ሲያስብ ክፋት ያለባቸውን ድርጊቶች በመስራት ይጠመዳል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካም ሰው

እዚህ ላይ “መልካም” የሚለው ቃል ጻድቅ ወይም መልካም ሥነ ምግባር ያለው የሚለውን ይወክላል፡፡

መልካም ሰው

እዚህ ላይ “ሰው” የሚለው ወንድ ወይም ሴት የሆነን ሰው ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡-“መልካም ሰው” (ተባዕታይ ቃላቶች ሴቶችን ሲጨምር የሚለውን ይመልከቱ)

ከልቡ መልካም መዝገብ

እዚህ ላይ የአንድ ሰው መልካም ሃሳቦች በዚያ ሰው ልብ ውስጥ እንደሚቀመጥ እንደ መዝገብ ተደርጎ ተመስሏል፡፡ “ልብ” የሚለው ደግሞ የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በውስጡ ከሚያኖረው ከመልካም ነገር” ወይም “እርሱ ዋጋ የሚሰጣቸው መልካም ነገሮች” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

መልካም የሆነውን ያፈራል

መልካም የሆነውን ያፈራል ማለት መልካም ስራዎችን ይሰራል የሚለውን የሚያሳይ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልካም የሆነውን ይሰራል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በልቡ ካለው ከክፉ መዝገብ

x