am_tn/luk/06/41.md

2.4 KiB

በወንድምህ አይን ላይ ያለውን …. ለምን ታያለህ? በራስህ አይን ውስጥ ያለውን ግንድ ለምን አትመለከትም?

ኢየሱስ ይሄን ጥያቄ የጠየቀው ሰዎቹ የሌላን ሰው ኃጢአት ከመመልከታቸው በፊት የራሳቸውን ኃጢአት መመልከት እንዳለባቸው ለመሞገት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በራስህ አይን ውስጥ ያለውን ምሰሶ ትተህ በወንድምህ አይን ያለውን … አትመልከት” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በወንድምህ አይን ያለውን ጉድፍ

ይህ ዘይቤ ሌላ አማኝ የሚያደርጋቸውን ጥቃቅን ስህተቶችን ይወክላል፡፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጉድፍ

“ጠብታ” ወይም “ጉድፍ” ወይም “የአቧራ ብናኝ”፡፡ የሰው አይን ውስጥ ሊገባ የሚችል በጣም ትንሽ ነገርን የሚወክል ቃል ካለ እሱን መጠቀም ይቻላል፡፡

በወንድምህ

እዚህ ላይ “ወንድም” የሚለው ሌላ አይሁዊን ወይም በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምን ሌላ ሰውን ይወክላል፡፡

በራስህ አይን የሚገኘውን ግንድ

ይህ ዘይቤ የአንድ ሰውን ትልልቅ የሚባሉ ጥፋቶችን የሚወክል ነው፡፡ ግንድ በአንድ ሰው አይን ውስጥ ቃል በቃል ሊገባ አይችልም፡፡ ኢየሱስ አጋንኖ የሚያወራው አንድ ሰው የሰውን ጥቃቅን ጥፋቶች ከማየቱ በፊቱ የራሱን ትልልቅ ጥፋቶች መመልከት እንዳለበት አጽንኦት ለመስጠት ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ እና ግነት እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ግንድ

“ምሰሶ” ወይም “ሳንቃ”

በአይንህ …. ልትል ትችላለህ?

ኢየሱስ ይሄን ጥያቄ የሚጠይቀው ሰዎቹ የሰው ኃጢአት ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ በራሳቸው ኃጢአቶች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ለመሞገት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በአይንህ … ማለት የለብህም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)