am_tn/luk/06/17.md

1.4 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ምንም እንኳ ኢየሱስ በተለየ ሁኔታ በቀጥታ የተናገረው ለደቀ መዛሙርቱ ቢሆንም በአካባቢው ሆነው ሲሰሙ የነበሩ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡

ከእነርሱ ጋር

“ከመረጣቸው ከአስራ ሁለቱ ጋር” ወይም “ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር”

ሊፈወሱ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኢየሱስ እንዲፈውሳቸው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በእርኩስ መናፍስት ይሰቃዩ የነበሩ ሰዎችም ተፈወሱ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኢየሱስ በእርኩስ መንፈስ ይሰቃዩ የነበሩ ሰዎችንም ፈወሰ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በእርኩስ መናፍስት ይሰቃዩ የነበሩ

“በእርኩስ መናፍስት ይቸገሩ የነበሩ” ወይም “በክፉ መናፍስት ቁጥጥር ስር የነበሩ”

የመፈወስ ኃይል ከእርሱ ይወጣ ነበር

“ሰዎችን ለመፈወስ ኃይል ነበረው” ወይም “ኃይሉን ሰዎችን ለመፈወስ ይጠቀም ነበር”