am_tn/luk/06/09.md

1.1 KiB

ለእነርሱ አላቸው

“ለፈሪሳውያኑ አላቸው”

እጠይቃችኋለሁ በሰንበት ቀን ሕጉ የሚከለክለው በጎ ማድረግን ነው ወይስ ክፋትን፣ ነፍስን ማጥፋት ነው ወይስ ነፍስን ማዳን?

ኢየሱስ ይህንን ጥያቄ ለፈሪሳውያን የሚጠይቃቸው በሰንበት ቀን ሰው መፈወሱ ትክክል እንደነበረ ፈሪሳውያን እንዲያምኑ ለማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ የዚህ ጥያቄ ዓላማ መልስ ፍለጋ አይደለም፣ ይልቁንም እውነት እንደሆነ የሚያውቁትን ነገር እንዲያምኑ ለማድረግ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኢየሱስ “እጠይቃችኋለሁ” ይላል፣ ስለዚህ ይህ ጥያቄ እንደሌሎች መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች በአረፍተ ሃሳብ ቅርጽ ተቀይሮ መጻፍ የሚችል አይደለም፡፡ ይህ ጥያቄ የጥያቄነት ቅርጹን ጠብቆ መተርጎም አለበት፡፡ (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)