am_tn/luk/06/06.md

1.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ጻፎችና ፈሪሳውያን ኢየሱስ በሰንበት ቀን አንድ ሰውን ሲፈውስ ይመለከታሉ፡፡

አጠቃላይ መረጃ፦

ይህ ሌላ የሰንበት ቀን ሲሆን ኢየሱስም በምኩራብ ነበር፡፡

እንዲህ ሆነ

ይህ ሐረግ በታሪኩ ውስጥ አዲስ ክስተት መጀመሩን ያሳያል፡፡ (የአዲስ ሁነት መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

… ሰው በዚያ ነበር

ይህ በታሪኩ ውስጥ አዲስ ገጸ ባህሪይን ያስተዋውቃል፡፡ (የአዲስና የቀድሞ ተሳታፊዎች መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

እጁ የደከመ

የሰውየው እጅ መዘርጋት እንዳይችል ሆኖ ተጎድቶ ነበር፡፡ የሰውየው እጅ ቡጢ በሚመስል ሁኔታ ታጥፎ የነበረ እንደነበርና መታጠፉም ትንሽና የተሸበሸበ እንዳስመሰለው ይገመታል፡፡

እያዩ ይከታተሉት ነበር

“በትኩረት ኢየሱስን እየተመለከቱት ነበር”

ሊያገኙበት

“ማግኘት ፈልገው”

በሁሉም መካከል

“ከሁሉም ፊት።” ኢየሱስ ሰውየው ሁሉም ሰው ሊያየው በሚችልበት ቦታ ላይ እንዲቆም ፈልጎ ነበር፡፡