am_tn/luk/06/01.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፦

“እናንተ” የሚለው የድርጊት ባለቤት መግለጫ ባለ ብዙ ቁጥር ሲሆን ደቀ መዛሙርቱን ይወክላል፡፡ (የሁለተኛ መደብ ቅርጾች የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲህም ሆነ

ይህ ሐረግ በታሪኩ ውስጥ አዲስ ክስተት መጀመሩን ያሳያል፡፡ ቋንቋችሁ ይህን ማሳያ መንገድ ካለው እሱን መጠቀም ይመከራል፡፡ (የአዲስ ሁነት መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሻ

እነዚህ ሰዎች የበለጠ ስንዴ ለማብቀል ስንዴ ዘርተውባቸው የሚገኙ ሰፋፊ የመሬት ክፍልፋዮች ናቸው፡፡

የጥራጥሬ እሸት

ይህ ረዥም ሳር የሚመስል የአንድ ጥራጥሬ ተክል ጫፍ ላይ የሚገኝ የተክሉ ክፍል ነው፡፡ ሊበሉ የሚችሉና የበሰሉ የተክሉ ፍሬዎችን ይይዛል፡፡

ፍሬዎቹን በእጃቸው መሃል እያሹ

ይህን የሚያደርጉት የጥሬውን ፍሬዎች ለመለየት ነው፡፡ ይህ ግልጽ ተደርጎ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእጃቸው መሃል አድርገው ያሹአቸው ገለባውን ከፍሬው ለመለየት ነው (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰንበት ቀን ሕጉ የሚከለክለውን ነገር ለምን ታደርጋላችሁ?

ይህን ጥያቄ የጠየቁት ደቀ መዛሙርቱን ሕግን በመጣስ ሊከሷቸው ፈልገው ነው፡፡ ይህ በአረፍተ ሃሳብ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሰንበት ቀን ጥራጥሬ መቅጠፍ ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ይቃረናል” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ነገር ትሰራላችሁ

ፈሪሳውያን አንድ እፍኝ ጥራጥሬን አሽቶ መብላትን የሚያክል ትንሽ ድርጊትን ራሱ ስራ እንደመስራት ይቆጥሩ ነበር፡፡ ይህ በግልጽ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስራን እየሰራችሁ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)