am_tn/luk/05/37.md

2.2 KiB

አዲስ ወይን

“የወይን ፍሬ ጭማቂ።” ይህ ያልፈላ የወይን ጠጅን ይወክላል፡፡

አቁማዳ

እነዚህ ከእንስሳ ቆዳ የተሰሩ መያዣ ከረጢቶች ናቸው፡፡ “የወይን ከረጢቶች” ወይም “ከቆዳ የተሰሩ ከረጢቶች” ተብለው መጠራትም ይችላሉ፡፡

አዲሱ ወይን ቆዳውን ያፈነዳዋል

አዲሱ ወይን ሲፈላና ቆዳውን ሲወጥረው ያረጀውን ቆዳ ያፈነዳዋል ምክንያቱም መለጠጥ ስለማይችል ነው፡፡ ኢየሱስ ይናገር የነበረውን ያዳምጡ የነበሩ ሰዎች ስለ ወይን መፍላትና ይዞታ መጨመር የሚረዱ ሰዎች ነበሩ፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ወይኑ ይፈስሳል

ይህ በአድራጊ ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወይኑ ከከረጢቶቹ ውስጥ ወጥቶ ይፈስሳል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

አዲስ አቁማዳ

“አዲስ አቁማዳዎች” ወይም “አዲስ የወይን ከረጢቶች” ይህ ጥቅም ላይ ያልዋለ አቁማዳን ይወክላል፡፡

አሮጌ የወይን ጠጅ የሚጠጣ … አዲሱን የሚፈልግ

ይህ ዘይቤ የኃይማኖት መምህሮችን አሮጌ ትምህርት ከኢየሱስ አዲስ ትምህርት ጋር አነጻጽሮ ያቀርባል፡፡ የዚህ ንግግር ዋና ነጥብ የድሮ ትምህርትን መስማት የለመዱ ሰዎች ኢየሱስ የሚያስተምረውን አዲስ ትምህርት ለመስማት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አሮጌ ወይን ጠጅ

“የፈላ ወይን ጠጅ”

'አሮጌው ይሻላል' ይላልና

“ስለዚህም አዲሱን ወይን ለመሞከር ፈቃደኛ አይሆንም” የሚለውን መጨመር አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)