am_tn/luk/05/33.md

1.6 KiB

አሉት

“የኃይማኖት መሪዎቹ ለኢየሱስ … አሉት”

ከእነርሱ ጋር …. ሊያደርግ ይችላል?

ኢየሱስ ሰዎቹ ከዚህ ቀደም የሚያውቁትን ነገር ደግመው እንዲያስቡ በማለት ይሄንን ጥያቄ ይጠይቃቸዋል፡፡ ይህ በአረፍተ ሃሳብ መልክ መጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ ዕድምተኞቹ ጹሙ የሚላቸው ማንም የለም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የሰርጉ ታዳሚዎች

“እንግዶቹ” ወይም “ወዳጆች” እነዚህ ከሚያገባ ወንድ ጋር ሆነው አብረው ደስታውን የሚጋሩ ሰዎች ናቸው፡፡

የሙሽራው ዕድምተኞች እንዲጾሙ ማድረግ

መጾም ሐዘንን ማሳያ ነው፡፡ የኃይማኖት መሪዎቹ ሙሽራው አብሯቸው እያለ ዕድምተኞቹ ሊጾሙ እንደማይችሉ ገብቷቸዋል፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀን ይመጣል

“በቅርብ” ወይም “አንድ ቀን”

ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት

ኢየሱስ ራሱን ከአንድ ሙሽራ ጋር ደቀ መዛሙርቱን ደግሞ ከሚዜዎች ጋር በንጽጽር ያቀርባል፡፡ ዘይቤውን አያብራራውም ስለዚህ ትርጉም ላይ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ብቻ ዘይቤው ይብራራ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)