am_tn/luk/05/29.md

1.7 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

በድግሱ ላይ ኢየሱስ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጋር ያወራ ጀመር፡፡

በቤቱ

“በሌዊ ቤት”

በማዕድ አብረው ተቀምጠው

በግብዣ ላይ የግሪክ የአመጋገብ ዘይቤ መደገፊያ ባለው መቀመጫ ላይ ተጋድመውና በመቀመጫቸው በግራ በኩል ባለው ድጋፍ ላይ ትራስ አስቀምጠው እዚያ ላይ በመደገፍ ነበር። አማራጭ ትርጉም፡- “በአንድ ላይ ምመብላት” ወይም “በማዕድ መብላት” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለደቀ መዛሙርቱ

“ለኢየሱስ ደቀ መዛሙርት”

ከኃጢአተኞች ጋር ለምን ትበላላችሁ

ጻፎችና ፈሪሳውያን የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ከኃጢአተኞች ጋር አብረው መብላታቸውን ለመቃወም ይህንን ጥያቄ ይጠይቃሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከኃጢአተኞች ጋር አብራችሁ መብላት የለባችሁም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

… ከኃጢአተኞች ጋር አብራችሁ ትበላላችሁ ትጠጣላችሁም

ፈሪሳውያንና ጻፎች ኃይማኖተኛ ሰዎች ኃጢአተኛ ብለው ከሚያስቧቸው ሰዎች ጋር አብረው መሆን እንደሌለባቸው ያምኑ ነበር፡፡ “እናንተ” የሚለው ገላጭ ብዙ ቁጥር አመልካች ነው፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ባለጤናዎች … ሕመምተኞች

x