am_tn/luk/05/27.md

1.2 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ኢየሱስ ቤቱን ለቅቆ በወጣ ጊዜ ሌዊ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ቀረጥ ቀራጭን እንዲከተለው ጥሪ ያቀርብለታል፡፡ ሌዊ ባዘጋጀው ትልቅ ድግስ ላይ የኢየሱስ መታደም ጻፎችና ፈሪሳውያንን እጅግ ያናድዳቸዋል፡፡

እነዚህ ነገሮች ከተከሰቱ በኋላም

“እነዚህ ነገሮች” የሚለው ሐረግ ቀደም ባሉ ቁጥሮች ላይ የተከሰቱትን ነገሮች ይወክላል፡፡ ይህ አዲስ ክስተት መጀመሩን ያሳያል፡፡ (የአዲስ ሁነት መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

የቀረጥ ቀራጭ ተመለከተ

“አንድ ቀራጭን በትኩረት ተመለከተ” ወይም “አንድ ቀራጭን አጥብቆ ተመለከተ”

ተከተለኝ

አንድን ሰው “መከተል” ማለት የዚያ ሰው ደቀ መዝሙር መሆን ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ደቀ መዝሙሬ ሁን” ወይም “እንደ አስተማሪ ተከተለኝ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉንም ነገር ትቶ

“የቀራጭነት ስራውን ትቶ”