am_tn/luk/05/22.md

3.1 KiB

ያስቡ የነበሩትን ተረድቶ

ይህ ሐረግ የሚያሳየው እነርሱ ድምጽ ሳያወጡ እያሰላሰሉ እንደነበር ኢየሱስ ግን ይናገሩ የነበረውን ሳይሆን ያስቡ የነበረውን እንደተረዳ ያሳያል፡፡

በልባችሁ ይህን ለምን ትጠይቃላችሁ?

ይህ በአረፍተ ሃሳብ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በልባችሁ ውስጥ ስለዚህ ነገር ምንም አይነት ሙግት ውስጥ መግባት የለባችሁም” ወይም “ኃጢአትን ይቅር የማለት ስልጣን እንዳለኝ መጠራጠር የለባችሁም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በልባችሁ ውስጥ

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል የሰውን አእምሮ ወይም የውስጥ ማንነት የሚወክል ምትክ ስም ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የትኛው ይቀላል … ተነሳና ተመለለስ

ጻፎቹ እርሱ ኃጢአትን ይቅር የማለት ስልጣን እንዳለው ወይም እንደሌለው የሚያረጋግጥላቸው ነገር ምን እንደሆነ እንዲያስቡ ይህን ጥያቄ ይጠይቃቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ 'ኃጢአትህ ተሰረየችልህ' አልኩ፣ እናንተ 'ተነስና ተመላለስ' ማለት ይከብዳል ብላችሁ ታስቡ ይሆናል ምክንያቱም ሰውየውን መፈወስ መቻሌና አለመቻሌ በሰውየው ተነስቶ መሄድና አለመሄድ ይታወቅ ነበር፡፡” ወይም “እናንተ 'ተነስና ሂድ' ከማለት 'ኃጢአትህ ተሰረየችልህ' ማለት ይቀላል ብላችሁ ታስቡ ይሆናል፡፡ (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ማለት ይቀላል

እዚህ ላይ በንግግር ያልተገለጸው እንድምታ አንድ ነገር “መናገር ይቀላል ምክንያቱም ምን እንደተከናወነ ማንም ማወቅ አይችልም” ነገር ግን ሌላውን ነገር “መናገር ይከብዳል ምክንያቱም ሁሉም ሰው ምን እንደተከናወነ ያውቃል።” ሰዎች የሰውየው ኃጢአት ተሰርዮለት እንደሆነ ሰዎች ማየት አይችሉም፣ ነገር ግን ሰውየው ከተነሳና ከተራመደ እንደተፈወሰ ሁሉም ያውቃሉ፡፡ (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

እንድታውቁ

ኢየሱስ ለጻፎቹና ለፈሪሳውያኑ ነበር ሲያወራ የነበረው፡፡ “እናንተ” የሚለው የባለቤት መግለጫ ብዙ ቁጥርን ያመለክታል፡፡ (የሁለተኛ መደብ ቅርጾች የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

ኢየሱስ ስለራሱ ነበር የሚያወራው፡፡

እልሃለሁ

ኢየሱስ ይህን የተናገረው ለሽባው ሰው ነው፡፡ “አንተ” የሚለው የድርጊት ተቀባይ ገላጭ ነጠላ ቁጥር ነው፡፡