am_tn/luk/05/20.md

1.6 KiB

ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ … አለ

ኢየሱስ ሽባውን ሰው መፈወስ እንደሚችል ሰዎቹ እንደሚያምኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህን በግልጽ ማሳየት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኢየሱስም ሰዎቹ እርሱ ሰውየውን ሊፈውሰው እንደሚችል እንዳመኑ ሲረዳ እንዲህ አለው” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ሰው

ይህ ስሙን ከማያውቁት ሰው ጋር ሲነጋገሩ ሰዎች የሚጠቀሙት የተለመደ ቃል ነው፡፡ አግባብ የሌለው አነጋገር አልነበረም፣ ግን የተለየ አክብሮትም አያሳይም፡፡ አንዳንድ ቋንቋዎች ይህን ለማሳየት “ወዳጄ” እና “ጌታዬ” የመሰሉ ቃላትን ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

ኃጢአትህ ተሰረየችልህ

ይህ በገቢር ቅርጽ መጻፍ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይቅር ተብለሃል” ወይም “ኃጢአትህን ይቅር ብዬሃለሁ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህ ጥያቄ ማቅረብ ጀመሩ

“ስለዚህ ነገር ተወያዩ” ወይም “ስለዚህ ነገር ምክንያቶችን ሰጡ።” የጠየቁትን ጥያቄ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኢየሱስ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ስልጣን ያለው መሆኑንና አለመሆኑን መወያያት ጀመሩ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)