am_tn/luk/05/12.md

1.9 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ኢየሱስ ሌላ ስሙ ባልተጠቀሰ ከተማ ለምፃም ፈወሰ፡፡

እንዲህም ሆነ

ይህ ሐረግ በታሪኩ ውስጥ አዲስ ክስተት መከሰቱን ያሳያል፡፡

በለምጽ የተሸፈነ ሰው

“ቆዳው በለምጽ የተሸፈነ ሰው።” ይህ በታሪኩ ውስጥ አዲስ ገጸ ባሕርይን ያስተዋውቃል፡፡ (የአዲስና የቀድሞ ተሳታፊዎች መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

በፊቱ ተደፋ

እዚህ ላይ “በፊቱ ተደፋ” የሚለው ሰገደ የሚለውን ትርጉም የያዘ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ተንበርክኮ በፊቱ መሬቱን ነካ” ወይም “በመሬት ላይ ሰገደ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ፈቃድህ ከሆነ

“የምትፈልግ ከሆነ”

ልታነጻኝ ትችላለህ

እዚህ ላይ ሰውየው ኢየሱስ እንዲፈውሰው እየጠየቀው እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ በግልጽ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማንጻት ስለምትችል እባክህ አንጻኝ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አንጻኝ … ንጻ

ይህ ሥርዓታዊ ንጽህናን ያመለክታል፣ ሰውየው በለምጹ ምክንያት ንጹህ እንዳልነበረ መረዳት ይቻላል፡፡ ካለበት በሽታም ኢየሱስ እንዲፈውሰው እየጠየቀው ነበር፡፡ ይህ ግልጽ በሆነ መንገድ መቀመጥ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ካለብኝ ለምጽ ፈውሰኝ … የተፈወስክ ሁን” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለምጹ ለቀቀው

“ከዚያ ጊዜ ኋላ ለምጽ አልነበረበትም”