am_tn/luk/05/08.md

1.4 KiB

በኢየሱስ ጉልበት ላይ ወደቀ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “በኢየሱስ ፊት ተንበረከከ” ወይም 2) “በኢየሱስ እግር ስር ሰገደ” ወይም 3) “የኢየሱስ እግር ስር ባለው መሬት ላይ ተኛ፡፡” ጴጥርስ በአጋጣሚ አልወደቀም፡፡ ይህንን የክብር እና የትህትና ምልክት እንዲሆን ለኢየሱስ አድርጎታል፡፡ (ምሳሌያዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ኀጢአተኛ ሰው

እዚህ ላይ “ሰው” የሚለው ቃል “ጎልማሳ ወንድ” ለማለት እንጂ በይበልጥ አጠቃላይ ለሆነው “የሰው ልጅ” አይደለም፡፡

የተያዘ ብዙ አሳ

“ብዙ ቁጥር ያለው አሳ”

የስምዖን ባልንጀሮች

“አሳ በማጥመድ ንግዱ ውስጥ የስምዖን ባልንጀሮች”

ሰውን ትይዛለህ

አሳን የማጥመድ ምስል ክርስቶስን እንዲከተል ሕዝብን ለመሰብሰብ እንደ ተለዋጭ ዘይቤ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎችን ታጠምዳለህ” ወይም “ለእኔ ሰውን ትሰበስባለህ” ወይም “ሰዎች የእኔ ደቀ መዝሙር እንዲሆኑ ታመጣለህ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)