am_tn/luk/05/01.md

2.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ኢየሱስ በስምዖን ጴጥሮስ ጀልባ በጌንሳሬጥ ሀይቅ ላይ አስተማረ፡፡

አሁን ይህ ሆነ

ይህ ሀረግ የታሪኩ አዲስ ክፍል መጀመሩን ለማመላከት እዚህ ላይ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የአንተ ቋንቋ ይህንን የማድረግ መንገድ ካለው፣ እዚህ ላይ እርሱን ለመጠቀም ማሰብ ትችላለህ፡፡ (የአዲስ ሁነት መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርን ቃል ማዳመጥ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች 1) “እግዚአብሔር እነርሱ እንዲሰሙ የሚፈልገውን መልእክት ማዳመጥ” ወይም 2) “ስለ እግዚአብሔር የሆነውን የኢየሱስ መልእክት ማዳመጥ”

የጌንሳሬጥ ሀይቅ

እነዚህ ቃላት የገሊላን ባህር ይወክላሉ፡፡ ገሊላ በሀይቁ ምዕራብ ጎን ነው፣ የጌንሳሬጥ መሬት በምስራቅ ጎን ነበር፣ ስለዚህ በሁለቱም ስሞች ይጠራ ነበር፡፡ አንዳንድ የእንግሊዘኛ እትሞች ይህንን እንደ ትክክለኛ የውሀው አካል ስም “የጌንሳሬጥ ሀይቅ” ብለው ይተረጉሙታል፡፡

መረባቸውን እያጠቡ

አሳ ማጥመጃ መረባቸውን እንደገና ለአሳ መያዣነት ለመጠቀም እያፀዱ ነበር፡፡

ከጀልባዎቹ አንዱ፣ የስምዖን የነበረው

“የስምዖን ንብረት የነበረው ጀልባ”

ከመሬት ጥቂት አርቆ በውሀው ውስጥ እንዲያስቀምጥ እርሱን ጠየቀ

“ስምዖንን ጀልባውን ከባህር ዳርቻው ራቅ እንዲያደርገው ጠየቀ”

ተቀመጠ እና ሕዝቡን አስተማረ

መቀመጥ ለአስተማሪ የተለመደ ሁኔታ ነበር፡፡

ከጀልባው ውስጥ ህዝቡን አስተማረ

“ጀልባው ውስጥ እንደተቀመጠ ሆኖ ህዝቡን አስተማረ፡፡” ኢየሱስ ከባህር ዳርቻው አጭር ርቀት ላይ በሚገኘው ጀልባው ውስጥ ነበር እናም በባህር ዳርቻው ላይ ለነበሩ ሰዎች እየተናገረ ነበር፡፡