am_tn/luk/03/21.md

2.9 KiB

አያያዥ ሀሳብ፦

ኢየሱስ አገልግሎቱን የጀመረው በጥምቀቱ ነው፡፡

አጠቃላይ መረጃ፦

የቀደመው ጥቅስ ሄሮድስ ዮሐንስን ወህኒ ቤት አስገባው ይላል፡፡ በቁጥር 21 ላይ የጀመረው መግለጫ ዮሐንስ ከመታሰሩ በፊት የተከሰተ እንደሆነ ግልፅ ማድረግ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ዩዲቢ የሚባለው ትርጉም ቁጥር 21ን “ነገር ግን ዮሐንስ ወህኒ ቤት ከመግባቱ በፊት” ብሎ በመጀመር ግልጽ ያደርገዋል፡፡ (የሁነቶች ቅደም ተከተል የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ሆነ

ይህ ሀረግ በታሪኩ ውስጥ የአዲስ ክስተት ጅማሬን ያመላክታል፡፡ የአንተ ቋንቋ ይህንን ለማድረግ መንገድ ካለው፣ እርሱን እዚህ ላይ ለመጠቀም ማሰብ ትችላለህ፡፡ (የአዲስ ሁነት መግቢያ የሚለውን ይመልከቱ)

ህዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ

“ዮሐንስ ህዝቡን ሁሉ ባጠመቀበት ጊዜ፡፡” “ህዝቡ ሁሉ” የሚለው ሀረግ ከዮሐንስ ጋር የነበሩትን ህዝብ ያመለክታል፡፡ (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ

ይህ በገቢር/አድራጊ ቅርፅ ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዮሐንስ ደግሞ ኢየሱስን አጠመቀው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰማይ ተከፈተ

“ሰማይ ክፍት ሆነ፡፡” ይህ ከተራ የደመና መጥራት የበለጠ ነው፣ ነገር ግን ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ አይደለም፡፡ ምናልባትም በሰማይ ውስጥ ቀዳዳ ታየ ማለት ነው፡፡

መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ

“መንፈስ ቅዱስ በሰውነት ቅርፅ በኢየሱስ ላይ እንደ ርግብ ወረደ”

ድምፅ ከሰማይ መጣ

እዚህ ላይ “ድምፅ ከሰማይ መጣ” የሚለው ሰዎች በምድር ላይ ሆነው እግዚአብሔር ከሰማይ ሲናገር መስማታቸውን ይወክላል፡፡ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ተናገሮ እንደነበረ ግልፅ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ድምፅ ከሰማይ ተናገረ” ወይም “እግዚአብሔር ከሰማይ ኢየሱስን እንዲህ በማለት ተናገረ” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ልጄ

ይህ ለኢየሱስ አስፈላጊ ስም ነው፣ የእግዚአብሔር ልጅ፡፡ (ልጅ እና አባትን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)