am_tn/luk/03/17.md

1.5 KiB

መንሹም በእጁ ነው

“መንሽ ይዟል ምክንያቱም እርሱ ዝግጁ ነው፡፡” ዮሐንስ ክርስቶስ በህዝብ ላይ ለመፍረድ ስለመምጣቱ ሲናገር እርሱ የስንዴውን ፍሬ ከገለባው ለመለየት የተዘጋጀ ገበሬ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ ዝግጁ እንደሆነ ገበሬ በህዝብ ላይ ለመፍረድ ዝግጁ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መንሽ

ይህ የስንዴውን ፍሬ ከገለባው ለመለየት ስንዴውን ወደ አየር የሚበትን መሳሪያ ነው፡፡ ከባድ ፍሬዎች ወደ ታች ይወድቃሉ የማይፈለገው ገለባ ደግሞ በንፋስ ይወሰዳል፡፡ ከሹካ መሰል ማበጠርያ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

አውድማውንም ፈፅሞ ያጠራል

አውድማ የመውቃት ዝግጅት ላይ ስንዴው የሚከመርበት ቦታ ነበር፡፡ አውድማውን “ማጥራት” ፍሬዎቹን ወቅቶ መጨረስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእርሱን ፍሬዎች ወቅቶ መጨረስ”

ስንዴውን ይሰበስባል

ስንዴው የሚጠበቅ እና የሚከማች ተቀባይነት ያለው አዝመራ ነው፡፡

ገለባውን ያቃጥለዋል

ገለባው ለምንም ጠቃሚ አይደለም፣ ስለዚህ ሰዎች ያቃጥሉታል፡፡