am_tn/luk/03/14.md

1.2 KiB

እኛስ? እኛ ምን ማድረግ አለብን?

“እኛ ወታደሮችስ፣ ምን ማድረግ አለብን?” “እኛ” እና “ለኛ” የሚሉት ቃላት ውስጥ ዮሐንስ አልተካተተም፡፡ ወታደሮቹ ዮሐንስ ለሰተበሰበው ህዝብ እና ለቀረጥ ሰብሳቢዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንደተናገረ አመልክተዋል እነርሱም እንደ ወታደሮች ምን እንደሚያደርጉ ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ (አግላይ እና አካታች “እኛ” የሚለውን ይመልከቱ)

ማንንም በሐሰት አትክሰሱ

ወታደሮቹ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ በሰዎች ላይ ሐሰተኛ ክስ እያዘጋጁ የነበረ ይመስላል፡፡ ይህ በትክክል ሊገለፅ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በተመሳሳይ መንገድ፣ ከእነርሱ ገንዘብ ለማግኘት ማንንም ሰው በሀሰት አትክሰሱ” ወይም “ንፁሁን ሰው ህገወጥ ነገር ሰርቷል ብላችሁ አትናገሩ”

ደመወዛችሁ ይብቃችሁ

“በክፍያችሁ የረካችሁ ሁኑ”